Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30996
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

አዳብና በጢያ ታሪካዊ ቦታ!! ሰብኛ በተት ዬሁን!!

Post by Horus » 22 Sep 2022, 00:00

እድሜዋ የገፋ ሴት ባል ፍለጋ ስትንቀዠቀዥ ያዩ እናቶቻችን 'በግርዝና አዳብና' ብለው ይተርታሉ! ያም ማለት በእርጅና አዳብና መውጣት ማለት ነው ! ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኧ እንደ ማለ ነው ። ጉርዝ ማለት ሽማግሌ ማለት ነው። ሽማግሎች ችግር ለመፍታት ሲቀመጡ ግርዝና ቶነሙም ሽምግልና ተቀምተዋል ይባላል። የአዳብና ዋነኛ አላማ ሚስት የምትሆን ቀንዠ (ልጃገረድ) ወይም ባል የሚሆን ጉልማሳ (ጎረምሳ) ለመተዋወቅ ነው ። ገረ (ገረድ) ከ13/14 አመት በላይ የሆነች ሴት ልጅ ስትሆን ቀንዠ ለትዳር የደረሰች ሴት ናት ። መስቀል ጎረ ጎረ ማለት ላቅመ አዳም የደረስንበት መስቅል ማለት ነው ። ልብ በሉ መስቀል ማለት አዲስ አመት ማለት ነው። ጉልማሳ ምስ (ባል) ለመሆን የደረሰ ወንድ ልጅ ማለት ነው።