Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Thomas H
Senior Member
Posts: 12612
Joined: 27 Jan 2007, 16:30
Location: Kaliti
Contact:

Must See : የኢትዮጵያ የከፍታ ዘመን በማስረጃ

Post by Thomas H » 20 Mar 2022, 10:10

ይህ የሆነው በደቡብ ክልል ጌዴዮ ዞን ዲላ ዙሪያ ጪጩ ጤና ጣቢያ ነው።
ነገሩ እንዲህ ነው ፥በአልጋው ላይ ያለችው ወላድ ስምረት ጥላሁን ትባላለች ። ባሳለፍነው ሳምንት በቤቷ ውስጥ ሆና ምጧ ይመጣና ቤተሰቦቿ አንቡላንስ ጠርተው አከባቢው ላይ ወዳለ ጤና ጣቢያ ይወስዷታል። በሰላም ተገላገለች ከዚያ በኋላ ነው እንግዲህ በምታዩት ሁኔታ መፀዳጃ ቤት ውስጥ ያሳረፏት!!
በጣም የሚያሳዝነው ወላዷ ማዬት የተሳናት በመሆኗ ወዴት እንዳስገቧት አላወቀችም ነበርና ያለችበት ቦታ ጠረኑ ሲያውካት ምንድነው ብላ ቤተሰቦቿን ትጠይቃለች። እነሱም "ቦታው ቆሻሻ ስለሆነ ነው" ከማለት ወጪ ያብራሩላት ነገር አልነበረም። ቤተሰቦቿ ይህን ያደረጉት ያለችበት ቦታ መፀዳጃ መሆኑን በመግለፅ የሞራልና የስነ ልቦና ጉዳት እንዳይደርስባት በማሰብ ነበር።
የወላዷ እህት በስልክ እንደገለፀችልኝ ከሆነ እንዴት እንዲህ አይነት ነውር ትሰራላችሁ በማለት ለጤና ጣቢያው ሃላፊዎች ጥያቄ ብታቀርብም ከሃላፊዎቹ ያገኘችው ምላሽ ዛቻና ማረስፈራሪያ ብቻ ነው። ይህን የሚያሳዝን የሰብአዊ መብት ረገጣ ለማን ነው አቤት የሚባለው? የሚገርመው ደግሞ ለዚህ ማዋለጃ ክፍል እድሳት 148 ሚሊዮን ብር ወጪ ሆኗል ::

by Tigist Tantu