Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Kuasmeda
Member+
Posts: 6387
Joined: 26 Mar 2015, 08:47

ደቤ- ደፋሩ አህያ!!!!

Post by Kuasmeda » 19 Mar 2022, 21:12

በልጀነቴ ለመጀመሪያ ግዜ የሸውራራ ሰው አይን ያየሁት ከገጠር ከቤተሰቦቹ ጋር የመጣ ዘመዳችንን ነበር።ፊት ለፊት አይኑን ማየት ስለማይቻል ከተለያየ አቅጣጫ ቢሞከር ይስተካከል መስሎኝ ልጁን እያዟዟርኩ አበሳውን አሳየሁት።እንደውም የባሰ እየተሸነቋቆረ ግራ አጋባኝ። የመጨረሻው ሙከራ እሱን አቁሜ ተንጋልዬ ሽቅብ ማየት ነበር አልተሳካም።በርግጥ እኩዮቼን አስተባብሬ ተሸክመን ንጠነው ለማስተካከል ሞክረን ነበር። አልሆነልንም፡፡

እሱም የዋዛ አልነበረምና ነገሩ ሲገባው፡ እስኪለምድ ሲያደባ ቆይቶ በደህና ስድብ ያጥረገርገን ጀመር። ባየን ቁጥር ቀድሞ ይሳደባል። እኔ ድሮም ቢሆን እንግዳ ነገር አግኝቼ ምርምር ብጤ አደረኩበት እንጂ ምንም ቅያሜ ስላልነበረኝና ረጃጅም፣ የማልረዳቸው ቃላት ስለበሩ አልመልስለትም ነበር ። አንዱን ቀን ጥቃት የማትወደዋ እህቴ ለምን ሲባል ነው ስድባችሁን ዝም ብላችሁ የመትጠጡት ብላ ጠየቀች? ድህረ ታሪኩ ሳይገባት መመለስ አስቸጋሪ ነበር።

''ያው ሌላ ቦታ እያየ ስለሚሳደብ ለኛ አይመስለንም።'' አልኩ

ታዲያ እሱ እንደሚያደርገው ሌላ ቦታ እያያችሁ አትሰድቡትም??? አለች ብሽቅ ብላ! በኋላ ላይ ነገሩን ስታጣራ ግን በደህና ኩሩኩም አበሰለችን።

እና አሁን እኝህን ሰውዬ ምን ብለን እንክሰስ? እውነት እንዲናገሩ እንናጣቸው ወይስ ወደ ካድሬነት እናዟዙራቸው? እንደሆነ ሰው አሁንም አባታችን እያለ ያቆላምጣቸዋል። የሃይማኖት ተቋማት የታቦት ማደሪያ መሆናቸው ቀርቶ የፖለቲካ ሆነዋል። በጣም የተቸገርነው ግን መእምኑ በሚለበሱት ልብስ ብቻ እየለካ የሸፈጣቸው ግዳይ መሆኑ ነው።ማስረዳትም መነጋገርም ይከብዳል። የእምነት እዳ ከባድ ስለሆነ በመስቀል ተደብቀው ከሚመጡ ተኩላዎች የዋሆችን ማዳን

ይቸግራል። ተቸገርነ፣ ተጠበብነ

የመቀሌ አስተዳዳሪ የነበረው ሃለቃ ጸጋዬ በዋልድባ ገዳም መነኩሴ ተመስሎ ለበዙ አመታት ተቀምጧል። ላለፉት 30 አመታት ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ የኤሪትሪያና የኢትዮጵያን ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያን ከውጪም፣ከውስጥም አገር ሆነው መእምኑን ሲያምሱ የቆዩት የተግሬ ካድሬዎች ቀሳውስት ተመስለው ነው። ፖለቲካ መሆኑ ቢነገራቸውም የማይሰሙ መእምናን፡ ጭራሽ ሌላ ቦታ የሚያይ ሸውራራ ጳጳስ ሲሆን ደሞ ነገሩን ያባብሰዋል።ጵጵስናው እንጂ ሴራው ሰለማይታይ !!

አሁን እስኪ ካልስና አህያ ወሰዱብን ብሎ ነገር አለ? በቁጥር የሚታወቁ 120ሺህ የተደፈሩ አሉ ካሉን የማይታወቁት መታወቅ ቢጀምሩ ስንት ሊደርሱ ነው።

ደግነቱ ጳጳስ ነኝ ሲል የነበረው ሰውዬ ደቤ- ደፋሩ አህያ መሆኑን እራሱ ሲናገር መረጃ ለማቀበል ይመቻል። እኛ ምን ቸገረን! እኛም ሌላ ቦታ እያየን እንደ አሮጌ

ዳንቴል ጉዱን እንተረትራለን።(በሰው አይን ለማሾፍ ሳይሆን ለማያያዝ ነው)

ኦ! አንድ ወደል አህያ እስከራቅምቦው መውሰድ ይቀረናል።ደቤ-ደፋሩን
ይቀጥላል

ኩራታችን ሰራዊታችን!

ዓወት ንሓፋሽ!

የጭነት አህያ ፎቶ፡ ናቅፋ ፕሬስ
የደቤ ደፋሩ አህያ ፎቶ፡ ከራሄል ይህደጎ ፌቡ
Meadi Guasot