Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

"HR 6600: TPLF is shrewd buyer. It bought multimillionaire senators Malinowski, Sherman & Rep Meeks for $11k" PP's Walta

Post by sarcasm » 18 Mar 2022, 13:02

አሳሪው ረቂቅ ሕግ - “HR 6600”
Walta Media and Communication Corporate



ለረቂቅ ህጉ ጠንሳሽ ለኒውጀርሲው ሴናተር ቶም ማሊኖውስኪ 2 ሺሕ ዶላር፣ ለካሊፎርኒያው ብራድ ሼርማን 6 ሺሕ ዶላር እና ለኒው ዮርኩ ግሪጎሪ ሚክስ 2 ሺሕ 900 ዶላር መክፈሏ ነው በመረጃው የተቀመጠው፡፡


መጋቢት 9/2014 (ዋልታ) ስድስት የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት አሳሪ የሆነውን HR-6600 ረቂቅ ሕግ አሜሪካ እንድታጸድቅ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡
እነዚህ ኢትዮጵያ ጠል አቋም ካላቸው ኃይሎች ጋር የተሰለፉት የኮንግረስ አባላት ለዓላማቸው ማስፈጸሚያ የእጅ መንሻ እንደተከፈላቸውም ተገልጿል፡፡
በኒውጀርሲው ሴናተር ቶም ማሊኖውስኪ መሪነት የተጠነሰሰና ለአሜሪካ ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ የቀረበ ረቂቅ ሕግ ነው “Ethiopian stabilization, peace and democracy act” ወይም “HR-6600!”
የኮንግረስ አባል ከሆኑት የኒውጀርሲው ቶም ማሊኖውስኪ በተጨማሪ፣ የካሊፎርኒያዎቹ ያንግ ኪምና ብራድ ሼርማን፣ የኒው ዮርኩ ግሪጎሪ ሚክስ፣ የሮድ አይላንድሱ ዴቪድ ሲሲሊን እና የቴክሳሱ ማይክል ማካውል ያዘጋጁት ረቂቅ ሕግ በኮንግረሱ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል፡፡
ረቂቅ ሕጉ ተቀባይነት አግኝቶ የሚጸድቅ ከሆነ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እንዲሁም የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤታቸው በኢትዮጵያ ላይ አሳሪ ህጎችን ለመጣል ሥልጣን ያገኛሉ፡፡
ይህም ማለት የዓለም ባንክና አይኤምኤፍ ለኢትዮጵያ የሚሰጡትን ብድር እስከ ማስከልከል የሚደርስ ዕርምጃ የአሜሪካ መንግሥት ሕጉን ተገን አድርጎ ሊወስድ ይችላል፡፡
በሌላም በኩል HR-6600 አሜሪካ ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የደኅንነትና የንግድ ድጋፍ እንድታቆም እንዲሁም አገሪቱ ከዓለም ዐቀፍ የፋይናንስ ተቋማት እርዳታና ብድር እንዳታገኝ ለማድረግ የተዘጋጀ ረቂቅ ሕግ ነው።
ይህ አሳሪ ህግ በረቂቁ ያካተታቸውን ቁልፍ ጉዳዮች ስንመለከት በመጀመሪያ ኢትዮጵያን የሚያዳክም እና በአፍሪካ ቀንድ አለመረጋጋትና ቀውስ እንዲፈጠር የሚያደርግ ከመሆኑም ባሻገር በፋይናንሱ ዘርፍ ኢትዮጵያ የምታገኘውን የብድር፣ ዕርዳታና መሰል ጥቅማ ጥቅሞች ማስቀረትን ያለመ ነው፡፡
በኢንቨስትመንት ዘርፍ ደግሞ ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ዓለም ዐቀፍ ልማት ፋይናንስ ኮርፖሬሽኖች ጋር ያላትን ግንኙነት በማገድ ኢንቨስትመንቶችን እና የገንዘብ ልውውጦችን የማስቆም አቅም አለው።
ረቂቅ ህጉ መሰረታዊ መብቶችንም ያግዳል፤ የኢትዮጵያ ዲያስፖራዎችና አጋሮች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዳያደርጉም ሆነ ገንዘብ እንዳይልኩ ይከለክላል፡፡
በተጨማሪም የኢሚግሬሽን ገደቦችንም ያካተተው ይህ ረቂቅ ሕግ የቪዛ አመልካቾችን እና የወደፊት የዲቪ ማመልከቻዎች መሰረዝንም የሚያካትት ነው።
HR 6600 በኢትዮጵያ ስላለው ሁኔታ ከኢትዮጵያ መንግሥትም ሆነ በአሜሪካ ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ጋር ምክክር ሳይደረግበት እንዲጸድቅ ግፊት መደረጉ ግልጽ አድሏዊነትን የሚያሳይ ነው፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት ለሰላም ያለውን ቁርጠኝነት አሳይቷል፡፡ ለዚህ ደግሞ የፖለቲካ እስረኞችን መፍታቱ፤ ሁሉንም ያሳተፈ አገራዊ ውይይት ለማድረግ ኮሚሽን ማቋቋሙ እና መሰል ተግባራቶቹ ማሳያዎች ናቸው፡፡
ነገር ግን ቶም ማሊኖውስኪ ያረቀቁት ይህ ሕግ ኢትዮጵያ ለሰላም ያላትን ዝግጁነት ችላ ያለ ከመሆኑም በላይ፤ ለረጅም ጊዜ የቆየውን የኢትዮጵያና የአሜሪካ ግንኙነት ከግምት ያላስገባም ጭምር ነው፡፡
እነዚህ ኢትዮጵያ ጠል አቋም ካላቸው ኃይሎች ጋር የተሰለፉት የኮንግረስ አባላት ለዓላማቸው ማስፈጸሚያ የእጅ መንሻ እንደተከፈላቸውም እየተገለጸ ነው፡፡
ይህም የኮንግረስ አባላቱ የአሸባሪዎች ዓላማን ከማስፈጸምና ከመደገፍ ባሻገር የኢትዮጵያ ሰላም ምናቸውም እንዳልሆነ በማያሻማ መልኩ የሚያረጋግጥ ነው፡፡
በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች የሚገኙ የአሸባሪው ቡድን ትሕነግ ደጋፊዎችና አባላት አሁንም ኢትዮጵያን ለማፍረስ “HR-6600“ን ከማስረቀቅ እስከ ማስጸደቅ እየደከሙ ነው፡፡

ሚራክል ናይን የተሰኘ የመዋቢያ ዕቃዎች አምራች ኩባንያ ባለቤትና የሽብር ቡድኑ ደጋፊ ሊሊ ገሰሰ ለኮንግረስ አባላቱ የገንዘብ ድጋፍ ማድረጓ ከታማኝ ምንጮች በተገኘ መረጃ ተረጋግጧል፡፡
ይህች ሴት ለረቂቅ ህጉ ጠንሳሽ ለኒውጀርሲው ሴናተር ቶም ማሊኖውስኪ 2 ሺሕ ዶላር፣ ለካሊፎርኒያው ብራድ ሼርማን 6 ሺሕ ዶላር እና ለኒው ዮርኩ ግሪጎሪ ሚክስ 2 ሺሕ 900 ዶላር መክፈሏ ነው በመረጃው የተቀመጠው፡፡

ኢትዮጵያን በግልጽ ለመጉዳት የተዘጋጀው ይህ ረቂቅ ሕግ እንዳይጸድቅ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥትም ረቂቅ ሕጉ የሁለቱን አገራት ግንኙነት ያላገናዘበና ኢ ፍትሐዊነት የተስተዋለበት መሆኑንም ማስገንዘብ ይጠበቅበታል፡፡
ሁሉም ኢትዮጵያዊ ይህ አሳሪ ህግ እንዳይጸድቅ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ በትዊተርና መሰል ማኅበራዊ የትስስር ገፆች ጠንካራ እንቅስቃሴ ማድረጉ የሚጠበቅ ሲሆን በእጅጉ አስፈላጊም ነው፡፡
Please wait, video is loading...
https://www.facebook.com/wmccwaltamedia ... 0369633368

Sam Ebalalehu
Member
Posts: 3639
Joined: 23 Jun 2018, 21:29

Re: "HR 6600: TPLF is shrewd buyer. It bought multimillionaire senators Malinowski, Sherman & Rep Meeks for $11k" PP's W

Post by Sam Ebalalehu » 18 Mar 2022, 13:19

I don’t think in the current congressional calendar, it will come to the full floor for a debate. In the next election , the Republicans will more likely take the speakership, and the hope that HR. 6600 will even be discussed in the foreign relations committee let alone in the full house is misplaced.

Post Reply