ESAT added 2 new photos.
1 min ·
መረጃ
ባህርዳር ከቅዳሜ ጀምሮ መግቢያዋና መውጫዋ በጥብቅ ፍተሻ ላይ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። በተለይ በህዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች ላይ ተሳፋሪን በሙሉ በማስወረድ ፍተሻ እየተደረገ ሲሆን ጸረ ሰላም ሀይሎች ሰርገው ገብተዋል የሚል ስጋት መኖሩን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ወደ አዲስ አበባ መውጪያ ድባቄ መድሃኒዓለም ቤተክርስቲያን አጥገብ የተተከለው ኬላ ዋና የፍተሻው ቦታ እንደሆነ ታውቋል። ወደ ጎንደር መውጫ አባይ ማዶ፡ ወደ አዴት መንገድ ሰባጣሚት ቀበሌ ላይ ጥብቅ ፍተሻ ከሚካሄድባቸው አከባቢዎች የሚጠቀሱ ናቸው።
https://www.facebook.com/ESATtv/photos/ ... 99/?type=3