Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum


መጪው ጊዜ ያስፈራው የሕወሃት አገዛዝ ከአማራ አካባቢና ሌሎች የኢትዮጵያ አምራች አካባቢዎች ከፍተኛ የእህል ክምችት ወደ ትግራይ እያስገባ ነው

Postby Abdisa » 24 Dec 2017, 16:02የሕወሃት አገዛዝ ከፍተኛ የእህል ክምችት ወደ ትግራይ እያስገባ ነው


Image

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 12/2010)


በኢትዮጵያ ሕዝባዊ ተቃውሞ የከፋ ደረጃ ይደርሳል በሚል የሕወሃት አገዛዝ ከፍተኛ የእህል ክምችት ወደ ትግራይ እንዲገባ እያደረገ መሆኑ ተነገረ።

መጪው ጊዜ ያስፈራው የህወሃት መንግስት ቀደም ሲልም ግዙፍ የእህል ጎተራ በማስገንባት እህል ሲያከማች መቆየቱ ይታወሳል።

አሁን ደግሞ ተጨማሪ እህል ከአማራ አካባቢና ሌሎች የኢትዮጵያ አምራች አካባቢዎች ከአርሶ አደሩ በርካሽ ዋጋ እየገዛ ወደ ትግራይ እያጓጎዘ መሆኑ ታውቋል።

የትግራይ ክልል ብዙ እህል በማምረት የሚታወቅ አካባቢ አይደለም።

በኢትዮጵያ በሕወሐት አገዛዝ ዘመን ለበርካታ ጊዜ ድርቅ ሲያጋጥም ግን በአካባቢው የእሕል እጥረት የሚባል ነገር ተከስቶ አያውቅም።

ምክንያቱ ደግሞ የሕወሃት አገዛዝ ያለውን ስልጣንና አቅም መነሻ በማድረግ ከፍተኛ እህል ከአማራና ከተለያዩ የኢትዮጵያ አምራች አካባቢዎች እየገዛ ስለሚያከማች መሆኑን የኢሳት ምንጮች ይናገራሉ።

ቀደም ሲል አምባሰል የሚባለው የብአዴን ድርጅት እህል ወደ ትግራይ በማጓጓዝ ተባባሪ ነበር።

እህሉን ከገበሬዎች በመግዛት በኩል ደግሞ መርከብ አምራቾች የስራ ማህበር የቅባት እህሎችን ጨምሮ ዋነኛ ተቋም ሆኖ ሲያገለግል ቆይቷል።

የመርከብ አምራቾች የስራ ማህበር አመራሮች ከምስራቅ ጎጃም የትኖራና ብቸና እንዲሁም ከምዕራብ ጎጃም ቡሬና አቸፈር እንዲሁም ባህርዳር ትላልቅ መጋዘኖችን በማዘጋጀት እህል ገዝቶ ወደ ትግራይ ሲልክ ቆይቷል።

በአሁኑ ጊዜ ደግሞ በኢትዮጵያ ያለው ሕዝባዊ ተቃውሞ ያስፈራው የሕወሃት አገዛዝ በደደቢት ብድርና ቁጠባ ተቋም አማካኝነት ከ2 ቢሊየን ብር በላይ ብድር ለነጋዲዎች ተሰጥቶ እህል እንዲገዛ ወስኗል።

የሕብረት ስራ ማህበራት እህልን በርካሽ ዋጋ ገዝተው በጉናና ትራንስ ትራንስፖርቶች አማካኝነት ወደ ትግራይ እንዲያጓጉዙ እቅድ ተይዟል።

ይህ ብቻ አይደለም በአማራ ክልል ከፍተኛ የባህር ዛፍ እንጨት ወደ ትግራይ እየተወሰደ መሆኑም ነው የተገለጸው።

ባህር ዛፉንም በመርከብ አምራቾች ስራ ማህበር በኩል ሲያጓጉዝ መቆየቱ ይታወሳል።

አሁን ደግሞ የአማራ አርሶ አደሮችን እህል በሕብረት ስራ ማህበራት አማካኝነት በርካሽ ዋጋ እሕል ገዝተው በመጋዘን እያስቀመጡ መሆኑ ታውቋል።

ይህ በመጋዘን የተቀመጠ እሕልም ወደ ትግራይ ሲያጓጉዝ ሕዝቡ ተቃውሞውን በማሰማት በተሽከርካሪ ላይ የተጫነውን እህል ከጭነት አውርዶ እንዲከፋፈልና እንዲያስቀረው ጥሪ በመደረግ ላይ ነው።


Image

ImageRe: መጪው ጊዜ ያስፈራው የሕወሃት አገዛዝ ከአማራ አካባቢና ሌሎች የኢትዮጵያ አምራች አካባቢዎች ከፍተኛ የእህል ክምችት ወደ ትግራይ እያስገባ ነው

Postby Abdisa » 24 Dec 2017, 16:37A few days ago, the Adwa native who calls himself "Awash" shared his legitimate fears about his TPLF regime's UN General Assembly vote in favor of the resolution rejecting President Trump's recognition of Jerusalem as Israel's capital, which he said will deprive his native Tigray of the US food aid it desperately needs for its survival.

Now that Tigray has landed on Trump's naughty list, and it no longer enjoys the largess of US aid, confiscating crops from poor Amhara and Oromo farmers to feed Adwa seems to be the easy "solution" to the self made debacle. The ሰርቆ አደር Agame Awash from Adwa may eat tonight, but its not that hard to predict what tomorrow holds for him. Bon Appétit.
:twisted:
Postby Degnet » 25 Dec 2017, 07:53


Give us back our beautiful land God,the beautiful land you and I know,enezihn gen zerachewn atfa.Postby Degnet » 25 Dec 2017, 08:10


It is your land,enersu enkuan hager alen yelalu,wef zerashPostby Degnet » 25 Dec 2017, 08:44


Leave my people,Amalek,the eternal enemy of God's people Israel,enezih znjero erasachew yasbubet,both of you are our enemiesPostby Degnet » 25 Dec 2017, 09:12


merkat endemetebek fenta endet edmeachehun stlefelfu tasalfut alachihu,nu wede Mekelle ena yeleflachihu.sichenkew rebel yadergal,safty valve in technical matters.Think about yoursef and help others if you can,that is paradise.nebsachehun yemarew elalehu enji lela ladrglachehu yemchelew yelem sew negn/amara sibal christian ymeslegn neber,ke Maxi endemayew gen aydelem,yekefawn tetenkeku,sew yale Egziabher mewut new.tinish fkir slalegn new endih yemlew.Kerenite,I am gone Alhamduleilah,Egziabher yemesgen malet eyu.yemesgen ember ne Isaias ewn aytsrefen.mehret yewrdelu,nab lebu yemleso.Re: መጪው ጊዜ ያስፈራው የሕወሃት አገዛዝ ከአማራ አካባቢና ሌሎች የኢትዮጵያ አምራች አካባቢዎች ከፍተኛ የእህል ክምችት ወደ ትግራይ እያስገባ ነው

Postby Amara Sayint » 25 Dec 2017, 14:47


ወልዳ ባሳደገች
ተነከሰች ደማች
በሕሊና ቢሱ ጠብቶ አይጠግቤ አረመኔ
በእናት ጡት ነካሽ ሽለምጥማጥ ወያኔRe: መጪው ጊዜ ያስፈራው የሕወሃት አገዛዝ ከአማራ አካባቢና ሌሎች የኢትዮጵያ አምራች አካባቢዎች ከፍተኛ የእህል ክምችት ወደ ትግራይ እያስገባ ነው

Postby Bwendimu » 25 Dec 2017, 15:36


That is good for Amara farmers. They got business and business bring people together than constitution. You must welcome this as an opportunity and tell Amara farmers to take advantage of this huge demand. The motive should not be a concern of farmers. If you produce guns you sale to any one by disregarding where it ends. Tigires are going back to war and you think that is why they buy grain. Not really but this year harvest in Tigirai is not promising I fear as rain came late.Re: መጪው ጊዜ ያስፈራው የሕወሃት አገዛዝ ከአማራ አካባቢና ሌሎች የኢትዮጵያ አምራች አካባቢዎች ከፍተኛ የእህል ክምችት ወደ ትግራይ እያስገባ ነው

Postby Amara Sayint » 25 Dec 2017, 18:06


ኤሎሄ ኤሎሄ ትላለች
አንጋጣ እያየች
ልመና አይሉት አቤቱታ
እጆጇን ዘርግታ
ከርታታዋ እማማ
ደጏ እናት ጦቢያ ታማ
ታማ .... ታማ .....

Next Page


Return to Ethiopian News & Opinion

Who is online

Registered users: Bing [Bot], Google [Bot], pushkin