ንብረታቸው በእሳት ለወደመ የጎንደር ነጋዴዎች የገቢ ማሰባሰቢያ በጎንደር ሕዝብ ወደ እንቅሥቃሴ ተገብቷል።

ባለፈው ሣምንት የጎንደር የገበያ ማዕከል በእሣት ተለኩሶ የወደመ መሆኑ ይታወቃል። በዚህ የእሣት አደጋ ንብረታቸው የወደመባቸው ነጋዴዎች ብዛት ከ440 በላይ ሲሆኑ የወደመው ንብረት ግምት ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚሆን ይገመታል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ተጎጅ ነጋዴዎችን ለማገዝ የገቢ ማሠባሠቢያ ፕሮግራም ለማካሄድ አሥተባባሪ ኮሚቴዎች ተመርጠው የአፈጻጸም መርሃ ግብር ወጥቶ ወደ እንቅሥቃሴ ተገብቷል። ይህ የገቢ ማሠባሠቢያ ምንም አይነት ከመንግሥት ንክኪ የሌለው ሲሆን በአጭር ጊዜ ተግባራዊ ይሆናል ተብሎ ይገመታል። እንደ ኮሚቴው ሃሣብ ከሆነ በሚቀጥሉት 10 ቀናት ውሥጥ ቅድመ ዝግጅቱ ተሠርቶ ይጠናቀቃል ተብሏል።


ይህ በእንዲህ እንዳለ በጎንደር የሥራ ማቆም አድማ ይደረጋል ተብሎ እየተወራ ይገኛል። ይህ የሥራ ማቆም አድማ ከጎንደር ነጋዴዎች እውቅና ውጭ እንደሆነና የተጎዱትን ለመርዳት እንቅሥቃሴ በተጀመረበት ሣምንት መሆኑ ነጋዴዎችን ሁለተኛ እንዳያገግሙ የሚያደርግ ከመሆኑ አንጻር ሲታይ የሥራ ማቆም አድማው ከጎንደር ነጋዴዎች እውቅና ውጭ ያደርገዋል። በመጨረሻም የጎንደር ተጎጅ ነጋዴዎችን ሁሉም አገር ወዳድ ህዝብ የአቅሙን እገዛ እንዲያደርግና ወደ ቀድሞ ህይዎታቸው ይመለሡ ዘንድ እጁን እንዲዘረጋ ማሣሠብ እንወዳለን!!


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE