በአዲስ አበባ ቂሊንጦ የማጎሪያ ካምፕ ላይ በደረሰው የእሳት ቃጠሎ አደጋ የ23 ሰዎች ህይወት ማለፉን ወያኔ ገለፀ።

በአዲስ አበባ ቂሊንጦ የማጎሪያ ካምፕ ላይ በደረሰው የእሳት ቃጠሎ አደጋ የ23 ሰዎች ህይወት ማለፉን ወያኔ ገለፀ።ሌሎች ዘገባዎች ከአርባ ሰው በላይ ሞቷል ሲሉ የወያኔ ልሳን የሆነው ፋና ያወጣው ዘገባ ህይወታቸው ካለፈ ሰዎች መካከል በአደጋው ወቅት በመረጋገጥ፣ በጭስ በመታፈን እና በቃጠሎ የሞቱት ሰዎች 21 ሲሆን፥ ሁለት ታራሚዎች ደግሞ ለማምለጥ ባደረጉት ሙከራ ህይወታቸው አልፏል። በቃጠሎው የማረሚያ ቤቱ ሁለት ህንፃዎች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው ከአገልግሎት ውጪ መሆናቸውን አመልክቷል።ማረሚያ ቤቱ ቶሎ ተጠግኖ የተለመደ አገልግሎት መስጠት እንዲችል ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ በመሆኑን ያመለከተው ዘገባ ሌላ ግፍ በዜጎች ላይ ለማድረግ መዘጋጀቱን ያመለክታል።ዛሬ ጠዋት የወጡ ዘገባዎች እንደሚያሳዩት ሆን ተብሎ በወያኔ ሰርጎ ገብ ወታደሮች እስረኞች ላይ ጥይት ይተኮስ እንደነበር ይጠቁማል። #MinilikSalsawi

Image may contain: text, outdoor and nature

► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE