የወልቃይት፣የማይጸብሪና የጠለምት የአማራ መብት አስከባሪ የሆኑት አቶ ላቀው ደስታ ዳላስ ከተማ ውስጥ ቤተክርስቲያን እንዳይገቡ በወያኔዎች ተከለከሉ

  • አቶ ላቀው ደስታ በወልቃይት፣ጠገዴና ጠለምት የማንነትና የአማራ የመብት ጥያቄ ላይ ንቁ ተሳታፊና ልሳን በመሆን  ለዓመታት  ከሚታገሉት አንዱ ናቸው።
  • ብዙውን ጊዜ  በታወቁ የዜና ማሰራጫዎች ላይ አሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ፣በኢሳት፣በአዲስ ድምፅ ራዲዮና በአውስትራሊያ ኤስ.ቤ.ኤስ. ራድዮ ላይ በተደጋጋሚ በማቅረብ  በህወሃት ወያኔ የታፈነውን  የወልቃይትን ህዝብ ጥያቄ ለመላው ዓለም ኢትዮጵያውያን በማቅረብ ይታወቃሉ።
  • በአሜሪካ ድምፅ ራድዮ ከልዑል ራስ መንገሻ ስዩም ጋር ባደረጉት  ቃለ ምልልስ ሁለቱም ወልቃይ፣ጠገዴና ጠለምት የትግራይ ሳይሆን በጎንደር ክፍለ ሀገር የሚገኝ አማራ መሬት መሆኑን በሚረጋግጠው የታሪክ ማስረጃ በሰጡት ቃለ ምልልስ ይታወቃሉ።
  • ህወሃት እንደዚህ ዓይነት የወረደና ተራ ነገር ውስጥ እጁን ማስገባቱ ተስፋ መቁረጡንና እንዲሁም ውድቀቱ እየተፋጠነ በመሄድ ላይ ለመሆኑ አመልካች ነው የሚሉ በርካቶች ናቸው።

ጁላይ 23 ቀን 2016 በዳላስ ከተማ ውስጥ ከ30 ዓመት በላይ ንዋሪ የነበሩ ፣በማሕበረሰቡ በጣም የሚወደዱና የሚከበሩ እንዲሁም በህይወት ዘመናቸው ለቤተክርስትያንና ለማሕበረሰብ ሰፊ አገልግሎት ይሰጡ የነበረ በተለይም  ልጆች በመልካም ስነ ምግባር ታንፀው እንዲድያጉ የላቀ አገልግሎት በማድረግ የታወቁ የወይዘሮ በየነች የቀብር ስነ ሥርዓት የሚፈጸምበት  ቀን ነበር። አቶ ላቀው ደስታ የሰላሳ አመት ወዳጃቸው፣ ማህበርተኛቸውንና የእህታቸውን ቀብር ለመገኘት በአቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስትያን ቅጥር ጊቤ ተገኝተው ነበር። መኪናቸውን እንዳቆሙ በሶስት የትግራይ ተወላጆችና የህወሃት አባላት  ከመኪናቸው  ድረስ በመሄድ  “አንተ እዚህ ቤተ ክርስትያን አጥር ግቤ ልትገባ አትችልም ፣የግላችን  ንብረት ስለሆነ ውጣልን አለበዚያ ፖሊስ እንጠራለን”በማለት አስፈራርተዋቸዋል ።

የተረጋጋና መልካም ባሕርይ ያላቸው አቶ ላቀው ደስታ ስሜታቸውን ተቆጣጥረው “በየነች እህቴ ነች፡ በእርሷ ቀብር ለመሳተፍ ነው የመጣሁት፣ በእርሷ ፍታት ለመገኘት ማንም እንደ ማይከለክለኝ አውቀዋለሁ። ነገር ግን ከእናንተ ባለጌና ስድ አደግ ጋር በሚፈጠር  ግጭት የእህቴ በየነች የፍታት ስነ ሥርዓት  እንዲረበሽ ስለማልፈልግ ወደ ቀብሩ ቦታ እሄዳለሁ” በማለት የቤተክርስያኑን ቅጥር ግቤ ለቀው በመሄድ በሪስት ላንድ ቀብር ቦታ በመገኘት  ወዳጃቸውን በምሪትና በለቀሶ ቀብረዋል። በቤተክርያኑ ቅጥር ግቢ ጉዳዮን በቅርብና በሩቅ የሰሙ “በእግዚአብሔር  ቤት በመግባት  እህታችንን  ለመሰናበት ማንነታችን ከሆነ መስፈርቱ” ቀብር ቦታ እንሄዳለን  በማለት ወጠው ሲሄዱ ታይተዋል።

አቶ ላቀው ደስታ በወልቃይት፣ጠገዴና ጠለምት የማንነትና የአማራ የመብት ጥያቄ ላይ ንቁ ተሳታፊና ልሳን በመሆን  ለዓመታት  ከሚታገሉት አንዱ ናቸው። ብዙውን ጊዜ  በታወቁ የዜና ማሰራጫዎች ላይ አሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ፣በኢሳት፣በአዲስ ድምፅ ራዲዮና በአውስትራሊያ ኤስ.ቤ.ኤስ. ራድዮ ላይ በተደጋጋሚ በማቅረብ  በህወሃት ወያኔ የታፈነውን  የወልቃይትን ህዝብ ጥያቄ ለመላው ዓለም ኢትዮጵያውያን በማቅረብ ይታወቃሉ። ከሁሉ በላይ በአሜሪካ ድምፅ ራድዮ ከልዑል ራስ መንገሻ ስዩም ጋር ባደረጉት  ቃለ ምልልስ ሁለቱም ወልቃይ፣ጠገዴና ጠለምት የትግራይ ሳይሆን በጎንደር ክፍለ ሀገር የሚገኝ አማራ መሬት መሆኑን በሚረጋግጠው የታሪክ ማስረጃ በሰጡት ቃለ ምልልስ ይታወቃሉ።

በቅርቡ የወሃትት መንግሥት መልእክተኛ ሁኖ በሰሜን አሜሪካ ከስድስት ወራት በፊት የመጣው የአማራ ክልላዊ መንግሥት በዳላስ ቴክሳስ በመጣበት ጊዜ ሰአት “አቶ ላቀው ደስታ ቡድኑን እናንተ ለአማራው ህዘብ መብት፣ልማትና ነፃነት ይልቅ ለህወሃት የምታገለግሉ ሎሌዎች ናችሁ። አማራው ሲፈናቀልና ዘሩ ሲጠፋ ያልተከላከላቸሁ፣ የአማራው መሪት ለሱዳን ሲሰጥ ያልጮኻችሁ፣ የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ህዝብ በህወሃት በኃይልና በጉልበት በትግራይ ሲካለልና የዘር ማጥፋት ሲካሄድ ከህዋት ጋር የተባበራችሁ ስለሆነ እናንተ ስለ ልማትና ዲሞክራሲ ለማውራት የሞራል ብቃት የላችሁም” በማለት ያደረጉት ሙግት በወዳጅም በጠላትም እንዲታወቁ አድርጓቸዋል ። በተጨማሪ አቶ ላቀው ደስታ በዳላስና ፎርት ወርዝ የጎንደር ህብረት መሪ መሆናቸው በህዋትና በተላላኪዎች ዘንድ ጥርስ ተነክሶባቸዋል።

ከሁለት ሳምንት በፊት የወልቃይት የማንነት አስተባባሪ ኮምቴዎችንና መሪዎችን  ለማፈንና ለማሰር ከትግራይ ክልላዊ መንግሥት ተነስተው የፊዴራል ፖላስ መለያ ያለው የሸራ መኪና ይዘው የአማራው ክልላዊ መንግስትን ሳያሳውቁ ጨለማን ተገን አድርገው  ጭምብል አጥልቀው ለማፈን ባደረጉት ጥረት ጀግናው የጎንደር ህዝብ የወልቃይትና የአርማጭሆ ታጣቂዎች በወሰዱት እርምጃ በህዋት ሚዲያ ዘጠኝ ወታደሮች ተገደሉብን ሲል በትክክል ከቦታው በተገኘ ማስረጃ አንድ መቶ ሃምሳ የተግራይ አፋኝ ሰራዊት ተደምስሷል። በተጨማሪም ለህዋት የመረጃ ምንጭ በነበሩ ሁለት ነጋዴዎች ላይ በንብረታቸው ላይ ጥቃት በማድረስ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶቸዋል። ጀግናው የጎንደር ህዝብ በአራቱም ማእዘን በመጠራራት በህወሃት ትግሬዎች ያለበትን ጥላቻና በቃኝ ባይነት  ከቀላል እስከ ከባድ መሳሪያ በመያዝ በተኩስ፣በፉከራና በወታደራዊ ትርኢት አሳይቷቸዋል ። በተከታታይ የተያዙት ኮሚቴ አባላት ተለቀው ፣ የወልቃይት የጠገዴና የጠለምት ህዝብ የማንነት ጥያቄ ምላሽ ካልተሰጠ የህወሃት የመጨረሻው መቃብር ጎንድር ይሆናል ብለዋል። በዚህ እርምጃ የተደናገጠው ህዋት ወያኔ ተደጋጋሚ መግለጫና አሉባልታ አሰምቷል። ከሁሉ በላይ በአውሮፓና በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች በማህበራቸው አመካኝነት በጎንደር ህዝብ የተነሳው የማንነትና የነፃነት ንቅናቄ የሚስፈራቸው እንደሆነና መንግሥት ወታደራዊ እርምጃ እንዲወስስድ ተማፅነዋል። የአማራው ህዝብ ሲፈናቀል በቀጥታና በረቀቀ ሁኔታ በሆነ ደረጃ የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ህዝብ የዘር ማጥፋት ሲካሄድበት ድምፃቸውን አሰምተው የማያውቁ የትግራይ ሊህልቃን ዛሬ ለአፈናና ለግድያ በመጡ አፋኝ የትግራይ ሚሊሻዎች ላይ አርምጃ ስለተወሰደና በሁለት የትግራይ ጀሮ ጠቢዎች ንብረት ላይ የአደጋ ስለለረሰ አማራው ላይ ጦር ይዝመትብት ብለው መንጫጫታቸው እጅግ ያስተዛዝባል።
በዳላስ ቲክሳስ የሚገኘው በቄስ ታደሰ የሚመራው የአቡነ አረጋዊ ቤተክርስታያን  በሟቹ በአቡነ ጳውሎስ እገዛ የተቋቋመ ከቅድስ ሚካኤል ቤተ ክርስትያን ተገንጥሎ  በትግራይ ተወላጆች ብቻ  የተቋቋመ ቤተክርስትያን ሲሆን የመለስ ዜናዊንና አቡነ ጳውሎስን የሙት አመታት በየዓመቱ ይዘክራል። ከአቶ መለሰ ዜናዊ ሞት በኋላ ሀገሪቱ በአዲስ ጠቅላይ ሚኒስተር በአቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ  እየተመራች እያለ  በቅዳሴው ጊዜ
ስሙ የሚጠራው የመለስ ዜናዌ ነው።

የደብሩ አለቃ ቄስ ታደሰ ከመንፈሳዊና ከወንገጌል ባህሪቸው ይልቅ የተጋዳይነት ስሜታቸውና የፀረ አማራ ዝንባሌቸው ከፍ ይላል። በመሆኑም በአቶ ላቀው ደስታ ከአቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስትያን ውስጥ እንዳይገቡ ማድረግ ግለሰቦች በደመ ነፍስ የፈጠሩት ሳይሆን በደብሩ ከካህናት አስከ ህወሃት ካድሪዎች የተመከረበትና የተዘከረበት የበቀል እርምጃ ነው።ዓላማው አቶ ላቀውን በማበሳጨት ምናልባትም በጉልበት ተጠቅመው ለመግባት ቢሞክሩ ጠብ ጫሪ በማስመሰል በማህብረተሰቡ ለማሳጣት ራሳቸው ከሰው ራሳቸው መስክረው በፓሊስ  አስይዘው በእነሱ እምነት ለማዋረድና አንገት ማስደፋት ነበር። ሆኖም ያሰቡት ነገር ግን ህወሃትን በውል የሚውቁት  አቶ ላቀው በብልሃት ወጥመዱን አልፈውታል።

ከዚህ የምንማረው የወለቃይትን የጠለምትን የማይፀብሪ  የአማራን መብትና ነፃነት አሰከባሪዎች ብቻ ሳይሆን ለሀገሩ በሁሉም መስክ የሚታገል አገር ወዳድ ሁሉ የወያኔዎችን መሰሪ ተንሎል በንቃት መጠንቀቅ አለበት። በዚህ አጋጣሚ በማወቅ ሆነ ባለማወቅ የዚህ አምባገነን በተለይም የህወሃት ደጋፊና ተባባሪ የሆናችሁ የአማራ ማህብረተሰብ ተወላጆች  ልትነቁና ሰልፋችሁን ልታስተካክሉ ይገባችዃል ። ህወሃት በአማራ ህብረተሰብ የሚደርገው አፈና ግድያና ዘር ማጥፋት ጊዜው መሽቶበታልና የህወሃት የመጨረሻው መቃብር ጎንደር ላይ ሲሆን በዚህ የሞት ሽረት ትንንቅ ውስጥ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከጎኑ ሊሰለፍ ይገባል ።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

ከገሪማ ታፈረ፤ዳላስ፣ አሜሪካ


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE