ድርድር ፣ውይይት ፣መቅለስለስ የሕወሓት ማዘናጊያ ስልት ነው፤ወያኔን ማመን ቀብሮ ነው፤ቀብሮም ብቻ ሳይሆን አቃጥሎ አመድ አድርጎ ነው!

  • ድርድር ፣ውይይት ፣መቅለስለስ የሕወሓት ማዘናጊያ ስልት ነው
  • ወያኔን ማመን ቀብሮ ነው፤ቀብሮም ብቻ ሳይሆን አቃጥሎ አመድ አድርጎ ነው

Minilik Salsawi  ከአማራው ክልል በተለይ ከጎንደር የሚመጡ ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት ሕወሓት ድርድር፣ ውይይት እርቅን ሽፋን በማለት ተቅለስልሶ እያዘናጋ ወጣቶችን በማፈስ ላይ ነው። ባለፈው ጊዜ የኦሮሞ ተቃውሞን ተገን በማድረግ ወሮበላ ቡድን ኣደራጅቶ በሻሸመኔ የፈጸመውን የግድያ ጥቁር ሽብር በጎንደርና በሌሎች የኣማራ ክልል ከተሞች ላይ የማይደግምበት ምክንያት እንደሌለ እያሰላሰልን ዋስትናው ምንድነው ማለቱ ተገቢ ጥያቄ  ነው? ድርድር ፣ውይይት ፣መቅለስለስ የሕወሓት ማዘናጊያ ስልቶች ናቸው። ወያኔን ማመን ቀብሮ ነው። ቀብሮም ብቻ ሳይሆን አቃጥሎ አመድ አድርጎ ነው።የአማራው ሕዝብ መነሳት ለሕወሓት ትልቅ አደጋ ኣለው የአማራው ሕዝብ መንቀሳቀስ ለሕወሓት መጪ እቅድ ትልቁ ጋሬጣ ሲሆን ሕወሓትን ላትመለስ እንደሚቀብራት ይታወቃል።

በተደጋጋሚ የምናገረው ጉዳይ ነው።ወያኔ በፍጹም- በፍጹም- በፍጹም ኣይታመንም። ኢሕአዴግ ተሃድሶ አያስፈልገውም፣ በስብሷል መፍረስ አለበት::እኛ አይደለንም ራሳቸው አመራሮቹ ድርጅታቸው እንደበሰበሰ ከሟቹ ጀምሮ ተናግረውታል።አሁን ያለው አመራር ሰው ያልተረዳለት ነገር ቢኖር ራሱን የሚክበው በባዶ ነው:: ሕዝብን እያስገደለ የሚገኘው ያልተማሩ በፕሮፓጋንዳ የተሞሉ ያልሰለጠኑ ፖሊሶችን ከአንዱ ክልል ወደ አንዱ ክልል እየወሰድ ነው።ለመሆኑ ስንቶቻችን እናውቅ ይሆን ? 25 ሺህ የልዩ ሃይል ፖሊስ ሰራዊት ከሶማሊያ ከደቡብ ሱዳን እና ኦሮሚኛ ተናጋሪ ከሆኑ ኬንያውያን ተመልምለው ሰልጥነው ከፌዴራል እና ከክልል እንዲሁም ከአግኣዚ ሰራዊት ጋር ተደባልቀው ሕዝብ እየገደሉ ይገኛሉ አሁንም ስልጣንን ከሕወሓት ሚሊሻዎች ጋር በጋራ ይጠብቃሉ የተባሉ ከየቦታው እየተመለመሉ እየሰለጠኑ ይገኛሉ።ከደህንነት ቢሮ የሚወጡ ጥቆማዎች አስደንጋጭ ናቸው።ወያኔ ጊዜ መግዣ ፋታ ማግኛ ማዘናጊያ ማደናበሪያ ያላቸውን የፕሮፓጋንዳ ስራዎች እየሰራ ነው።የወያኔን አካሄድ ጠንቅቀን ማወቅ አለብን ዝም ብሎ ፖለቲከኛ ነኝ አያሉ ማራገብ “አክቲቭስት ነኝ” እያሉ መብጠልጠል/ ማጦልጦል ጥቅም የለውም።ወያኔን ማመን ቀብሮ ነው።ቀብሮ ብቻ ሳይሆን አቃጥሎ አመድ አድርጎ ነው።ካልሆነ ጊዜ ገዝቶ እያዘናጋ የለውጥ ሃይሉን ወጣቶችን አመድ ለማድረግ ቆርጧል።

ሕወሓት በፖለቲካው እና በኢኮኖሚው ዘርፍ የማፊያ የወሮበላ ቡድን የሌቦች ስብስብ ነው።የራሱን ካልሆነ በቀር የሌሎች ክልሎች ይሁን የሕዝቦቻቸን የኢኮኖሚ እድገት በፍጹም ኣይፈልግም።ያኮላሻል ተስፋ ያስቆርጣል በሙስና እንዲዘፈቁ ያደርጋል ኣሰልሶ ያጠፋቸዋል። ሁሉም ነገር ስህተት ነው ብለው ራሳቸው አምነዋል ከተባለ እነዚህ ሰዎች ስልጣን የማለቁበት ምክንያት ምንድነው? የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን.. የኦሮሞና የኣማራ ሕዝብ ላይ ላይ የወሰዱት ድድብና የተሞላበት ግድያና ድብደባና እስር … የትራፊክ ሕግ … የጤና መድህን ዋስትና … ሁሉ ፖሊሲያቸው ስህተት ነው እያሉ እየተናገሩ ነው።በአገራችን ላይ አስተዳዳሪ ነን ብለው እስከተቀመጡ ድረስ ሃገርና እና ሕዝብን የሚመሩበት ፖሊሲ ስህተት እና ፉርሽ ከሆነ ምን እየጠበቅን ነው።ሕዝብ ላይ እየደነፉ ሕዝብ ላይ እያሾፉ ሕዝብን እየዋሹ ከዚህም አልፈው እየገደሉ እያሰሩ እያሳደዱ ይህ ስራችን ስህተት ነው እያሉ ደጋግመው እያደረጉት እኛ ግን ምን እየሰራን ነው? እነሱ ሰው ለመጨፍጨፍ በአንድነት ሲዘምቱ ደግመው ለለመዋሸው በአንድነት ሲደሰኩሩ እኛ ስለ ነጻነታችን ምን እየሰራን ነው?እስከመች እንዘናጋለን ? ድር ቢያብር አንበሳ ያስር አንድ እንጨት ብቻውን አይነድም።#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Minilik Salsawi's photo.

► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE