ከሸዋ ክፍለ ሐገር ሕዝብ ለጀግናው የጎንደር-በጌምድር ክፍለ ሐገር ሕዝብ የተላከ መልዕክት

ይድረስ ለጀግናው የጎንደር-በጌምድር ክፍለ ሐገር ሕዝብ፤

ጠላትም ወዳጅም እንዲያውቅልን የምንፈልገው በጎንደር ክፍለ ሐገር ውስጥ የአማራ ህዝብ እየከፈለ ያለውን መስዋዕትነት ማለትም አማራነቴን አልነጠቅም ተጋድሎ ለሁላችንም ለአማራነት ማረጋገጫ በመከፈል ላይ ያለ መስዋትነት እንደሆነ እንገነዘባለን። እኛ የሸዋ አማራዎች ከሽማግሌ እስከ ወጣት አካላችን ሸዋ ቢሆን ላንዲት ደቂቃ እንኳን ጎንደርን ብሎም መላውን የአማራን ግዛት የማናስብበት ጊዜ የለም።

የጎንደር ጀግኖች ሆይ ከጎናችሁ ነን። እስከመጨረሻው የአማራ የነጻነት ቀን አብረን ለመዋደቅ ዝግጁ ነን። ዝግጅትም ጨርሰን እንገኛለን። እናንተን ለማገዝ ጎንደር መሄድ ሊያስፈልገንም ወይም ላያስፈልገንም ይችላል። በወያኔ ላይ የምናደርገው እንቅስቃሴና የመልስ ምት መጠኑም ሆነ ስፋቱ በጎንደር ውስጥ በሚኖሩት ነባራዊ ሁኔታዎች ላይ እንዲሁም የጎንደር ህዝብ በሚያደርግልን ጥሪ ይወሰናል። ስለሆነም እኛ የሸዋ አማራዎች በተወካዮቻችን አማካይነት ለሁለት ቀናት ባንዲት ታሪካዊ ቦታ ተሰባስበን ከልብ ቆርጠን የትግል መላ መተን ከጎንደር አማራዎች ጎን መሆናችንን እናረጋግጣለን ።

ትግሉን የጎንደር አማሮች ጀመሩት እንጂ እኛም ጫፍ ላይ ነበርን። ወያኔ የስልጣን ማማ ላይ ከተቆናጠጠበት ከሃያ አምስት ዓመት አንስቶ የሸዋ ህዝብም ላይ በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ በደልና ግፍ በወያኔ ተፈጽሞብናልና። ጠላትም ሆነ ወነ ወጃጅ ሊያውቀው የሚገባው ታላቅ ቁም ነገር ጎንደርን ለመታደግ የሸዋ አርበኞች ጎንደር ድረስ መሄድ ላያስፈልጋቸው ይችላል። እጃችን መዳፍ ውስጥ ያሉ ወያኔዎችን አመድ የሚያረጉ ከባድ የእርምጃ ስልቶች አሉን። በወያኔዎች ላይ የምንወስዳቸው እርምጃዎች አብዛኛዎቹ በተለያዩ ቦታዎችና በሁሉም ቦታዎች በተመሳሳይ ሰዓትና ደቂቃ የሚደረጉ ሳይታሰቡ እንደ እሳተ ገሞራ የሚፈነዱ ናቸው። ሁላችንም በስብሰባችን ፍጻሜ በወያኔ ላይ የማያዳግም አይቀጡ ቅጣት ለመውሰድ ተማምለናል።

አጥንታችንና ደማችን የሆነው የጎንደር ሕዝብ በወያኔ ላይ በወሰደው እርምጃ በጣም የኮራን ስንሆን በሸዋ “የነ አይምሬ” መነሳሳት ከምንግዜውም በላይ ያስደስታል። ከጎጃምና ወሎ ክፍላተ ሐገሮች ጀግኖችም ጋር እየተመካከርን ነው።እያነጠለ ከሚጨርሰን አብረን ተነስተን እንደ አባቶቻችን በአንድ ላይ በመሆን ቅኝ ገዢውንና ወራሪውን  ወያኔን እናወድመዋለን!

ሐምሌ ፲፪ ቀን ፪ሺ፰ ዓ.ም

ሸዋ፣ ኢትዮጵያ

 

 


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE