ለትግራይ ክልል የሕወሓት ባለስልጣናት 16.3 ቢልዮን ብር የተገዙ V_8 መኪኖች ጁብቲ ወደብ ደረሱ::

ጉድ በል ትግራይ … !!!
¥¥¥¥¥¥¥¥¥

የህወሓት ባለስልጣናት 16.3 ቢልዮን ብር የጨረሰ ኣንድ ግዙፍ ፕሮጀክት ይዘው መጥተዋል።

የንፁ መጠጥ ውሃ ችግር ለመቅረፍ፣ ወጣቶች ከስደት የሚገላግልና የስራ እድል ለመፍጠር የሚጠቅም ፋብሪካ ለመገንባት፣ ገበሬው ለመስኖ ልማት ለመሰማራት፣ የመብራት ተደራሽነት ለማስፋት የሚጠቅም ግድብ ለመገንባት ወዘተና ህዝቡ የበለጠ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ትላልቅ ስራዎች ለመስራት የተመደበ ኣይደለም።

16 ቢልዮን ብሩ ከዚ የበለጠ ጥቅም የሚሰጥ ከባድ ስራ ለመስራት የተመደበ ግዙፍ ብር ነው ¡¡¡¡ ኪኪኪ ይሉናል ህወሓቶች።

እስቲ ልንገራቹ …… ¡¡

እነ ዚህ ሌት ተቀን ደከመኝ፣ ሰለቸኝ ሳይሉ ህዝቡ በንቃት(በንቀት ኣላልኩም) እያገለገሉ ያሉት ከዞን እስከ ክልል የሚገኙ የህወሓት ከፍተኛ ካድሬዎችና መሪዎች ምቾታቸው እንዳይጎድል ተብለው(ለህዝቡ ጥቅም ሲባል) ተገዝተው ጁብቲ ወደብ የደረሱ በመቶ የሚቆጠሩ እጅግ ዘመናዊ V_8 መኪኖች ናቸው።

ይህ ብርና እነዚህ መኪኖች “ህወሓትና የትግራይ ህዝብ የኣንድ ሳንቲም ሁለት ገፆች ናቸው። ኣንዱ ካንዱ ልትለያቸው ኣትችልም ” የሚሉ ሃይሎች(ህወሓትም ይጨምራል) ዋነኛ ማሳያዎች መሆናቸው የሚያረጋግጡ ናቸው ¡¡¡¡¡

በ16.3 ቢልዮን ብር ዋጋ የተገዙ V_8 መኪኖች ለትግራይ ክልል ባለ ስልጣናት፣ ለማእከላዊ ኮሚቴ ኣባላት በሙሉ፣ የዞን ከፍተኛ ኣመራሮች፣ የድርጅት ከፍተኛ ባለ ስልጣናት የሚሰጡ ናቸው።

እነዚህ የV_8 መኪኖች ሲከፋፈሉ በሚደረገው ተሃድሶ የሚጠበቀው ንግግር ” መኪኖች የተገዙት ሰፊው ህዝብ የበለጠ ተጠቃሚ ለማድረግ ታሳቢ ተደርጎ ነው” የሚል ይሆናል።

የዘንድሮ ጉምበት 20 ልዩ የሚያደርገው የትግራይ ገዢዎች(ህዝብ ትግርኛ ተናጋሪ ደርጎች ይላቸዋል) በ16.3 ቢልዮን ብር V_8 መኪኖች ተገዝተው ከየጉንበት 20 ፍሬዎች ተካፋይ የሆኑበት በዓል ስለ ሆነ ነው።

የጉንበት 20 ፍሬ የ16.3 ብር V-8 መኪኖች በብዛት መገዛታቸው ነው።

ጉድ በል ትግራይ ………!

በኣሁኑ ሰዓት የህወሓት መሪዎች የሚሰሩት ፍፁም የማያውቁ፣ ማሰብ ያቆሙ ደንታቢሶች ሁነዋል እና ራስህ በሰለማዊ መንገድ ለሚደረገው ትግል ዝግጁ ኣድርግ።

እናንተ የትግራይ ወጣቶችም ህዝባቸው ስለ ረሱ የህወሓት መሪዎች መከላከላቹ ኣቁማቹ በረሃብና በችጋር ስለሚሰቃየው ህዝባቹ ኣስቡ፣ ታገሉ።

የእምባስነይቲ ህዝብ ትግሉን ጀምሮታልና ሁላችንም እንቀላቀልበት።

የደርግ ቋንቋው ብቻ ነው የተሸነፈው።

ነፃነታችን በእጃችን።

it is so.

Amdom Gebreslasie's photo.

► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE